ከጎሳው ውጭ ባፈቀረ ዘመዱ ሰበብ የተገደለው ሶማሊያዊ ጉዳይ ቁጣን ቀስቅሷል

Posted by

ሶማሊያዊው አህመድ ሙክታር ሳላህ የእህቱ ልጅ ከጎሳው ውጪ የሆነች ሴትን ሊያገባ ሲያቅድ አልተከላከልም በሚል በቁሙ እንዲቃጠል መደረጉ ቁጣን ቀስቅሷል።

የባንቱ ጎሳ አባል የሆነው የሳላህ የእህት ልጅ ከሌላ ጎሳ ሶማሊያዊት ጋር የምስጢር ግንኙነት ይጀምራል።

ከዚያም የልጅቱ ቤተሰቦቹ በድርጊቱ እጅጉን ተቆጥተው ልጃችንን መልስልን ቢሉምፍ ቅረኛሞቹ ሃገር ጥለው ይጠፋሉ።

ነገር ግን የልጅቱ አባት ፍቅር ይበልጣል ብለው ለጥንዶቹ ይሁንታ ይለግሳሉ፤ እናት እና ሌላው አዝማድ ግን አንገታችን ለካራ ይላሉ።

በዚህ ምክንያት ነው አህመድ ሙክታር ሳላህ በእህቱ ልጅ ምክንያት ሞጋዲሹ ከተማ ውስጥ በስለት ተውግቶ እና በህይወት እያለ በእሳት ተቃጥሎ የተገደለው።

ከድርጊቱ በኋላ ነው ፖሊስ የልጅቱን እናት እና ሌሎች በድርጊቱ እጃቸው አለበት የተባሉ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ሥር ያዋለው።

ዕለተ እሁድ በተፈፀመው የሳላህ ቀብር ላይ ቁጥሩ እጅግ የበዛ የሃገሬው ሰው ተገኝቷል።

አልፎም ለቤተሰቡ መርጃ ይሆን ዘንድ ሶማሊያዊያን የገንዘብ ማሰባሰብ መጀመራቸውም ተነግሯል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *